የኢራንና አፀፋፃ ኔታንያሁ እንዳሰቡት በቀላሉ የሚቋቋሙት እንዳልሆነ ሲታወቅ ግን የአሜሪካ መሪዎችን ጎትተዉ ከዉጊያዉ ጨመሩ።ፕሬዝደንት ትራምፕ ከምረጡኝ ዘመቻቸዉ እስከ በዓለ-ሲመታቸዉ፣ ከፕሬዝደንት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ እስከ ጆ ባይደን የነበሩ የአሜሪካ መሪዎችን በጦርኝነት ሲወቅሱና ሲከስሱ ነበር።ጦርነትን ለማስቆም ቃል ያልገቡበት ጊዜም አልነበረም።