የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ገበያ መር ከተደረገ አንድ ዓመት ሊሞላው ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ረቡዕ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ134 ብር ይሸጣል። ኢትዮ ፎሬክስ የተባለ የግል የምንዛሪ ተቋም ደግሞ አንዱን ዶላር በ155 ብር ከ90 ሳንቲም ይሸጣል።