ውጥረት ውስጥ የገባው የህወሓት እና የፌዴራል መንግስቱ ግንኙነት

Wait 5 sec.

በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ (ሕወሃት) መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ እየተባባሰ የሄደ መስሏል። ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን አስከፊውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት መግታት የቻሉት ሁለቱ ኃይላት ስምምነቱን አጽንተው ዘላቂ ማድረግ ግን ተስኗቸዋል።