በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ባለሥልጣኖቻቸውና የሩሲያ ባንኮች ብርቱ ማዕቀቦች ተጥለውባቸዋል። የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ 630 ቢሊዮን ዶላር ከማንቀሳቀስ ሲታገድ የሩብል ምንዛሪ አሽቆልቁሏል። አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረትና አጋሮቻቸው የሚወስዷቸው እርምጃዎች የሩሲያን ኤኮኖሚ ከዓለም አቀፉ ሥርዓት እንደሚገፋ ተንታኞች ይናገራሉ