የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ በኢትዮጵያ እና አባል አገራቱ ሰኞ ዕለት "ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ ሁሉም የምርጫ ክልሎች በቀጣይ ምርጫ የማካሄድ እድል እንዲያገኙ ተስፋ እናደርጋለን" አሉ። የምርጫውን ሒደት በይፋ ያልታዘበው ኅብረቱ፦ «አጠቃላይ ምርጫ መካሄዱን እንቀበላለን» ሲል ዛሬ ረቡዕ ባወጣው አጭር መግለጫ ጠቅሷል።