የሁለቱ ሀገራት ውዝግብ ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት ወደለየለት ጦርነት ባይሸጋገርም በአፍሪቃው ቀንድ አጠቃላይ ጦርነት እንዲቀሰቀስ የሚያደርግ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ መታየቱ እየተነገረ ነው።ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ጉዳዩን በውይይት እንዲፈቱ እያሳሰቡ ነው።