ማሕደረ ዜና፣ ቀይ ባሕር፤ በደም ቀልቶ ደም የሚገበርለት ባሕር

Wait 5 sec.

ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ሐገር በነበሩበት ዘመን ይዋጉ ነበር።30 ዓመት። ሁለት ሐገርም ሆነዉ ይዋጋሉ።የአሥመራና የአዲስ አበባ መሪዎች ያልተዋጉበት ጊዜ ከነበረ-አንድም-በ1990ዎቹ እንዳየነዉ «የጋራ ጠላት» የሚሏቸዉን መንግሥትን ወይም በ2013 እንደሆነዉ የመቀሌ ገዢዎችን ለመዉጋት የተወዳጁበት-ሁለትም አንዱ የሌላዉን ጠላት የሚያደራጁበት ነበር።