በትግራይ ክልል እየተደረጉ ያሉ ሰሞነኛ ስብሰባዎችና የነዋሪዎች ኹኔታ

Wait 5 sec.

በትግራይ ክልል በተለይ መቀሌ ውስጥ ተከታታይ ስብሰባዎች እየተደረጉ ነው። በስብሰባዎቹ የሚደመጡት መልዕክቶች ህወሓት ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት እየተካረረ ለመሄዱን ጉልህ ማሳያ ተደርጓል። የፌዴራል መንግሥት የሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን፣ ህወሓትን እና መሪዎቹን የሚነቅፉ ተከታታይ ዝግጅቶችን እያስተጋቡ ይገኛሉ።