የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ “አክራሪ” ባሏቸው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላትና በቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ገደብ ጥለዋል። የግጭትና የዲፕሎማሲ ተመራማሪ ነጋልኝ መኮንን፣ኢትዮጵያ ያለችበትን አጠቃላይ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ያላካተተ ያሉት ይህ የአሜሪካ እርምጃ ውጤት ያመጣል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።