የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአራት ክልል ውስጥ የሚገኙ የ24 የምርጫ ክልሎች ውጤትን ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ምርጫው ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20 ቀናት ውስጥ ውጤቶችን ከስር ከስር እያሳወቀ እንደሚያጠናቅቅም ነው ያመለከተው።