ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎች በየጊዜው ትግራይ ባሉ ኃይሎች ይፈጸማል” ሲሉ ወንጅለዋል። ዐቢይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በገደምዳሜ ስለ ጽምዶ ጠቀስ አድርገዋል። ይሁንና ህወሓት፣ ኤርትራና ሱዳን ቢተባበሩ እንኳ ለኢትዮጵያ “ሉዓላዊነት ቅንጣት ታክል ሥጋት” እንደማይሆኑ ገልጸዋል።