የኢትዮጵያን መንግሥት በጋራ ለመውጋት የተቀናጀ ተብሎ የሚነገርለት "ፅምዶ" የሚባለውን ጥምረት በተመለከተ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ልዩ ልዩ አቋሞች እየተንፀባረቁ ነው። የኤርትራ፣ የትግራይ እንዲሁም የአማራ ኃይላትን ያሰባሰበ ነው የሚባለው ይህ ቅንጅት "ወደ ከፍተኛ የትግል ደረጃ" ስለመድረሱ ከትግራይ በኩል በግልፅ እየተነገረ ይገኛል።