በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምት፣ ደጃጅ ሜዳ ወረዳ፣ በበየዳ እና በጃና ሞራ ወረዳዎች የክረምት ዝናብ ባለመጣሉ በርካታ ሰዎች ለራብ መጋለጣቸውን የጃና ሞራ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶ ቢሻው አለሙ ተናግረዋል። አቶ ቢሻው አክለውም በድርቁ ምክንያት የሰው ህይወት ማለፉን እና እንስሳትም መሞታቸውን ገልፀዋል።