በዛክሰን አንሃልት ግዛት በተካሔደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ከ44% በላይ ድምጽ በማግኘት እንደሚያሸንፍ መራጮች ድምጽ ሰጥተው ሲወጡ የተሰበሰበ አስተያየት አሳይቷል። የመራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት (CDU) በምርጫው ከተሰጡ ድምጾች 18.5% እንደሚያገኝ ይፋዊ ያልሆነው ውጤት አሳይቷል።