በጀርመኑ ዛክሰን አንሀልት ግዛት ምርጫ የጀርመን የሕገ መንግሥት ደኅንነት አስከባሪ መስሪያ ቤት ቀኝ ጽንፈኛ ብሎ የፈረጀው AfD በመጀመሪያ ደረጃ ውጤት 43.8 በመቶ ድምጽ ማሸነፉ ተረጋግጧል። ፓርቲው ከምክር ቤቱ 83 መቀመጫዎች 39ኙን በማሸነፍ የዛክሰን አንሀልት ጠ/ሚኒስትር የመሆን እድሉ የሰፋ መስሎ ነበር። መንገዱ ግን ቀላል አልሆነም።