30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከወራት በፊት ያከበረው ሪፖርተር አማርኛ፣ ዘ - ሪፖርተር እንግሊዝኛ እና የድርጅቱ የበይነ መረብ ሥርጭት አገልግሎት ከትናንት ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ "ላልተወሰነ ጊዜ" ታግዷል።

Wait 5 sec.

ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በሚባልበት ወቅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ጌታቸው ድንቁ ይህ 'እርምጃ "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚዲያ ምኅዳሩ ከመንግሥት አካባቢ ከሚወጣው መረጃ እና ትርክት የተለዩ ሐሳቦችን በነፃነት የማንሸራሸር ዕድሉ እየጠበበ እንደመጣ ጠቋሚ መሆኑን ለዴቼ ቬለ ገልፀዋል።