የቀጠለው የሞያሌ ግጭት እና ሰብዓዊ ቀውስ

Wait 5 sec.

የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ከተማዋ ሞያሌ ግጭት ከተከሰተ ከሁለት ሳምንታት በላይ ቢሆነዉም ግጭቱ ዛሬም ድረስ ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው። በአስተዳደር ወሰን ውዝግብ የጀመረው በከባባድ መሳሪያ ጭምር ታግዞ በቀጠለዉ ግጭት የሰዎች ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ኬንያ ተፈናቅለዋል፡፡