"በአገር ማፍረስ ሴራዎች" ተጠርጥረው በእሥር ላይ የሚገኙትና ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢሕአፓ አባል ፖለቲከኞች እና ጠበቃ ለቀጣዩ ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን ተቀጠሩ። ኢሕአፓ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለኢሰመኮ ጉዳዩን በደብዳቤ ያሳወቀ መሆኑን ገልጾ "ኹኔታው ተጣርቶ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥያቄ አቅርቧል።