ጠበቃቸው እንዳሉት ተጠርጣሪዎቹ እያንዳናቸው በ50 ሺህ ብር ማስያዣ የዋስትና መብታቸው ተፈቅዶላቸዋል። ፖሊስ ተከሳሾቹን "ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን እንደሽፋን በመጠቀም" ሥልጣን በኃይል ለመያዝ"በማሰብ ከህወሓት፣"ሌሎች ፀረ-ሰላም" ካያላቸው ኃይሎች ጋርና "ፅምዶ" ከተባለ አካል ጋር በመቀናጀት ተንቀሳቅሰዋል በሚልም ከተያዙ አንድ ወር አልፏቸዋል።