በኢትዮጵያ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት በአማካይ በቀን ከ9.2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊየን ሊትር ቀንሷል። ሀገሪቱ የኢራን ጦርነት ሲቀሰቀስ የገዛችውን 180,000 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ማስገባት አልቻለችም። በወር ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ለመደጎም መገደዱን የገለጸው መንግሥት ዜጎች “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክሯል።