ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ቀርቦ ብር የዶላር ተመን ይወርዳል ተብሎ ቢገመትም ያ አለመሆኑ የፍላጎቱ ጣሪያ መንካትን የሚሳይ ብለዋል የገንዘብ አስተዳደር ባለሞያው። ባንኮች በተለይም ከወርቅ ግዢ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ገንዘብ ስላከማቹ በቀላል የማይገኘውን ዶላር የመግዛት አጋጣሚ ሲያገኙ ገዝተው በማስቀመጥ ለደንበኞቻቸው ማቅረብ ይፈልጋሉም ብለዋል፡፡