የናይጄሪያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ሰኞ ዕለት በመቀሌ ያደረጉትን ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ገልጿል።የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ "የሁሉም መሪዎች ዓላማ መሆን አለበት" ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ "ይህንን ለማሳካት የሁሉም ወገኖች መግባባትና መደራደር ያስፈልጋል" ብሏል።