ህወሓት የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ለ6 ወር ያቋቋመውን ባለአደራ አስተዳደር "ሕጋዊነት ወይም ተፈጻሚነት እንደሌለው" በማለት ተቃውሟል። ከፌዴራሉ መንግሥት ጋር ግጭት ዉስጥ የገባው ህወሓት ከተቋቋመው ባለአደራ አስተዳደር ጋር የሚተባበር ማንኛውም ድርጅት የመንግሥት አካል ተደርጎ እንደሚቆጠር እና ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስቧል።