የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የጦርነት ሂደት ያለ ተጠያቂነት እንዲያስቀጥል ያደርጋል ያለው ጥምረቱ፣ አሜሪካ ጉዳዩን በሚመለከት ሚዛናዊና ገንቢ አቋም እንዲኖራት ጠይቋል።

Wait 5 sec.

የፌዴራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል የተመሠረተው ትብብር ለሕልውና የተባለው የፖለቲካ እና የትጥቅ ቡድኖች ስብስብ ቅዳሜ ዕለት በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተሰጠውን አስተያየት ተቃወመ። ማሮኮ ሩቢዮ ስም ሳይጠቅሱ "ተገንጣይ" ባሉት ኃይል በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ የድሮን ጥቃቶች መፈፀማቸውን አረጋግጠዋል።