ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በኢትዮጵያ “የጸጥታ ውጥረት መጨመር” እና ግጭት በሚደረግባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ “ማኅበሰረቦች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ” እንደሚያሳስበው አስታወቀ። የግጭቱ “ስፋትና የሚቆይበት ጊዜ” ስለማይታወቅ በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ “ለመገምገም ጊዜው ገና” እንደሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለዶቸ ቬለ ገልጸዋል