በትግራይ ክልል በሰው አልባ አውሮፕላን «ተከታታይና የተጠናከረ» ጥቃት መኖሩን ህወሓት መግለፁ

Wait 5 sec.

በትግራይ ክልል በተለይ ካለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) «ተከታታይ እና ተጠናክሮ የቀጠለ» ጥቃት እየተፈፀመ መኾኑን ህወሓት ገለፀ። የድርጅቱ ቃል ዐቀባይ እንዳሉት የድሮን ጥቃቶቹ በሰዎች መኖሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በአርሶ አደር መንደሮች እና ንጹሐን ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ነው።