የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ጨምሮ ሰባት ታጣቂ ቡድኖችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና የተባለ ጥምረት መመሥረታቸውን በይፋ አወጁ። ትብብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩትን መንግሥት በማስወገድ “አካታች የሽግግር መንግሥት” የማቋቋም ዓላማ አለው።