የትግራይ አማጽያን በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን መቆጣጠራቸውን የጸጥታ እና የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ፣ አክሱም እና ሽሬ የሚደረጉ በረራዎችን “በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት” አቋርጧል።