በእንግላዝኛው ምህጻረ ቃል አውሰም በመባል የሚታወቀው በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ ቀጣይ እጣ ፋንታ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ቆይቷል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው የሐምሌ ወር መጀመሪያ ይፋ ያደረገችው ድጋፍ የማቆም ውሳኔ ነው።