«የምርጫው ውጤት እንዲሁ በቀላሉ ችላ የምንለውና እንደወትሮው መቀጠል የምንችልበት አይደለም። ይኸን አናደርግም። በሰፊው ተወያይተናል። በእኛ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። እኔንም በግል ነክቶኛል። እውነቱን ልናገር ይኸ የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ በዓመታት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በበርካታ አስርት ዓመታት ውስጥ የደረሰበት ከባድ የምርጫ ሽንፈት ነው»