ታጣቂዎቹ ከአዲስ አባባ እና ከቡታጅራ የተነሱ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን ማስቆማቸውን የተናገሩት አንድ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን የሶዳ ወረዳ ነዋሪ “ የወረዳው ፖሊስ አባላት እና ሚሊሻዎች ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል ፡፡ በዚህም የፀጥታ አባላት በታጣቂዎቹ ተመተው ህይወታቸው ማለፉን አውቃለሁ “ ብለዋል ፡፡