ስማቸው እንዳይጠቀስ የገለጹት የትግራይ የሰላም አዛዥ እንደሚሉት ዕዳጋ ሓሙስ ከገቡት የኤርትራ ወታደሮች ወደ አፅቢ ወንበርታ አቅጣጫ በ2 የጭነት መኪኖች ተጭነው በሚጓዙበት ወቅት በድሮን ተመተዋል። ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ የሚዋጋው ታጣቂ ቡድን አመራር ተፈጽሟል ያሉትን የድሮን ጥቃት ዶይቼ ቬለ በገለልተኝነት አላረጋገጠም።