የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል በ38 ምርጫ ክልሎች [ማለትም ሙሉ በሙሉ] እንዲሁም በአማራ ክልል በ8 ምርጫ ክልሎች ሰኞ ግንቦት 24 ምርጫ እንደማይደረግ ገለፀ። ይህ ማለት ግን በእነዚህ አካባቢዎች «ሁል ጊዜ [ምርጫ] ሳይደረግ ይቀራል ማለት ሳይሆን» አስቻይ ኹኔታ ሲኖር ሥራው ወደፊት ይቀጥላል ተብሏል ።