ይሁንና የዋሽግተን ባለሥልጣናት እንዳሉት ከስምምነት ጫፍ ላይ መድረሳቸዉን አላረጋገጡም።ኢራኖች እንደሚሉት የሆርሙዝ ወሽመጥ የኢራንና የኦማን ጉዳይ እንጂ ዩናይትድ ስቴትስን አይመለከትም።የኑክሌር ጉዳይም ወደፊት ድርድር እንዲደረግበት ተግባቡ እንጂ አሜሪካኖች እንዳሉት በእስካሁኑ ድርድር ስምምነት አልተደረገበትም