የዓለም የጤና ድርጅት ትናንት ከቀትር በኋላ በሰጠው መግለጫ የኤቦላ ተሐዋሲ ስርጭት ሁኔታ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ውስጥ ፍጥነቱን እየጨመረ መሆኑን አመልክቷል። የአፍሪቃ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ተቋም ሲዲሲም የተሐዋሲውን ሁኔታ አሳሳቢ ብሎታል።