የኢትዮጵያ ሰባተኛ ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ

Wait 5 sec.

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ሰኞ ለሚካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአካባቢው የምርጫ ቦርድ ማስተባበሪያ አስታወቀ። በኦሮሚያ መንግስትን በትጥቅ የሚወጋው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ምርጫውን በመንቀፍ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የክልሉ ፖሊስ ምርጫው በፀጥታ ችግር እንዳይፈተን በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።