ግጭት ያልራቀው የአማራ ክልል ወጣቶች ስለ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ምን ይላሉ?

Wait 5 sec.

የቆቦው ወጣት “ሀገርም እየፈረሰች ቢሆን ምርጫ ግዴታ ነው” የሚል ዕምነት አለው። የደሴው ነዋሪ “በጫካ ውስጥ ያሉት አካላቶች የመጨረሻው ግባቸው ሊሆን የሚችለው ምርጫ ነው” ብሎ ይጠብቃል። ከቅርብ ርቀት ተኩስ የሚሰማው የመካነ ሰላም ወጣት በአካባቢው በሚካሔደው ግጭት ምክንያት “መጀመሪያ ሰላም ሳይኖር ምርጫ አለ እንዴ?” ሲል ይጠይቃል።