የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሰሞኑን ሰባተኛ ተከታታይ የስልጣን ዘመናቸውን የሚያስጀምራቸውን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። የበርካታ ምስራቅ አፍሪቃዉኢን የፖለቲካ መሪዎች በጦር ከታመሰች ሀገር በወታደራዊ መለዮ የተገለጡት ሰው እንደምን አራት አስርት ዓመታትን በስልጣን ላይ ቆዩ ፤ ዩጋንዳንስ ከየት አንስተው የት አደረሱ ሲሉ ይጠይቃሉ ።