በአማራ ክልል በሴቶች ላይ የሚደርሰው ወሲባዊ አካላዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቃት አስከፊ መሆኑ ተገለጸ። በተያዘው የበጀት ዓመት ብቻ ከ17 ሺህ በላይ ሴቶች የተለያዩ ጥቃቶች ሰለባ መሆናቸውን የክልሉ የሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታዉቋል። ለጥቃቱ መባባስም በታጣቂ ኃይሎች መካከል ያለዉ ግጭት ነዉ ተብሎል።