ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት(ኦነግ-ኦነሰ)ን ሴቶችን በጅምላ በመድፈርና የማሰቃየት ወንጀሎችን ጨምሮ በበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከሰሰ፡፡ተቋሙ “የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በኦነሰ ተዋጊዎች የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃት፣ ከፍርድ ውጭ ግድያና የማሰቃየት ወንጀል ሊመረምሩ ይገባልም”ብሏል፡፡