ዛሬ(ማክሰኞ) ምሽት ዳላስ ላይ ፤ ፈረንሳይ እና ምባፔ ወይስ ስፔይን እና ያማል ?

Wait 5 sec.

የአሜሪካው የዳላስ ስታዲየም የወቅቱን የአውሮጳ እና የዓለም እግር ኳስ ከዋክብትን ባቀፉ ሃገራት መካከል የሚደረገውን ፍልሚያ ያስተናግዳል። መላው ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የ2026ቱ ፊፋ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በስፔን እና በፈረንሳይ መካከል ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ይደረጋል።