በኢትዮጵያ የዩናትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ በመጓዝ የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ ስለተደቀኑ ፈተናዎች መምከራቸው ተነገረ። አምባሳደሩ ወደ መቀሌ ለመጓዝ ያሰቡት ቀደም ብሎ ቢሆንም ክልሉ ላይ ባንዣበበው ስጋት ምክንያት በሦስት ሳምንታት ዘግይተዋል።