ከአንዳንድ አካላት የጉባኤው የተሳታፊዎች ምልመላ ሂደትና ገለልተኛነቱ ላይ ጥያቄ መኖሩን ጠቅሰን የራሳቸውን ልምድ የጠየቅናቸው ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ የመጡት ትንሳኤ በቀለ "እኔ ስወከል አላወኩም። ቀኑ ከደረሰ በኋላ ተመርጠሻል፣ እኛን ትወክያለሽ፣ ችግራችንን ታስረጃለሽ ብለው መረጡ፣ ሕዝቡ ከመረጠኝ ብየ የሕዝቡን አደራ ይዤ ነው የመጣሁት።"ብለዋል።