ከሰሜን ሱዳን ጥግ ራስ ካሳር እስከ ደቡብምሥራቅ ግርጌ ጀቡቲ ጠረፍ ወይም ባብ ኤል መደብ ወሽመጥ አጠገብ ራስ ዱሜራ ድረስ የሚወርደዉ የኤርትራ የባሕር ድንበር ከ1000 ኪሎ ሜትር ይበልጣል።ጥያቄዉ ግን ከባሕር ወሽመጡ በተቃራኒ የሚዋሰነዉን ግዛት የሚቆጣጠረዉ ማነዉ-ነዉ።«የመን ናት» መለሱ ኤርትራዊዉ የፖለቲካ ተንታኝ አብዱረሕማን ሰይድ