በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥትና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መካከል የሚደረገዉ ዉዝግብና ቁርቁስ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። ህወሓት በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት የተሰየመዉን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቆጣጠረ ወዲህ ከመንግሥት ጋር የነበረዉ ቂም እየተካረረ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። ህወሓትም ወጣቶችን ለዉትድርና እያስገደደ ነዉ ተብሏል።