በደቡባዊ የኢትዮጵያ ድንበር ከተማ ሞያሌ የቀጠለውን ግጭት ሸሽተው ወደ ኬንያ የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁትር እየጨመረ ነዉ። በአሁኑ ወቅት ለተፈናቃዮች በቂ ምግብ እና መጠለያ ለማቅረብ ፈታኝ እየሆነ መምጣቱን የኬንያ መርሳ ቤት ግዛትና ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አመልክተዋል። የአካባቢዉ ቀዉስ ”እጅግ አሳሳቢ” ተብሏል።