ኢትዮጵያ ያስጠለለቻቸው ስደተኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ"ማካተት" ፍኖተ- ካርታ፤ በተለይ በጋምቤላ ክልል ለሚኖሩ ስደተኞችና ተቀባይ ማኅበረሰቦች በጎ የፖሊሲ አቅጣጫ መሆኑን የቀድሞ የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ተናገሩ። ፍኖተ-ካርታው በዓለም አቀፍ የስደተኞች አስተዳደር ሕግ መሠረት ከተተገበረ አልፎ አልፎ የሚታየውን ግጭት ይቀንሳል ተብሏል።