የየመን ሁቲ ታጣቂዎች፣ የባብኤል ማንደብ መተላለፊያን ለመዝጋት እንዲዘጋጁ በኢራን የቀረበው ጥሪ የአፍሪካ ቀንድ አገራትን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ተጋላጭ የሚያደርግ ነው ሲሉ የፀጥታ ጉዳዮች ተንታኝ ተናግረዋል። ቀይ ባሕር ኢላማ የሚደረግ ከኾነ፣ ቀጥተኛ ያልኾነው ተጽዕኖ ኢትዮጰያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ሊታይ ይችላልም ተብሏል።