በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን አርሲ-ሺርካ ወረዳ ቢርቦና ጮሌ ቀበሌ ቅዳሜ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ከቆሰሉ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ሕይወታቸው እንዳለፈ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። በጥቃቱ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በአብያተ ክርስቲያናት ተጠልለው እንደሚገኙ ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።