በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ለተፈፀመው ግድያ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማሕበረ ቅዱሳን ጠየቀ። ማሕበሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ግብር የሚተዳደሩ ያላቸው መገናኛ ዐውታሮች በተደጋጋሚ ተፈጽሟል ያለውን ጥቃት እንዳልሰሙ ማለፋቸውን አጥብቆ አውግዟል።የፖለቲካ ድርጅቶች ግለሰቦችና ይመለከተናል ያሉ ኹሉ ግድያውን እንዲቆም ተጠያቂነትም እንዲኖር እየጠየቁ ነው።